ዥማር ሁለገብ ኢንዱስትሪ አ.ማ የሚፈርሰው በንግድ ሕጉ በተደነገገው መሠረት በመሆኑ ይህንኑ ተግባር የሚያስፈጽም የሂሣብ አጣሪ (Liquidator) ቀጥሮ ማሠራት ይፈልጋል

Tender
< Back

ዥማር ሁለገብ ኢንዱስትሪ አ.ማ የሚፈርሰው በንግድ ሕጉ በተደነገገው መሠረት በመሆኑ ይህንኑ ተግባር የሚያስፈጽም የሂሣብ አጣሪ (Liquidator) ቀጥሮ ማሠራት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታቂያ

ዥማር ሁለገብ ኢንዱስትሪ .

የማሕበሩ ባለአክስዮኖች በታህሣስ 25 ቀን 2012 . ባካሄዱት 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ኩባንያው እንዲፈርስ በከፍተኛ ድምጽ ወስነዋል፡፡ ማሕበሩ የሚፈርሰው በንግድ ሕጉ በተደነገገው መሠረት በመሆኑ ይህንኑ ተግባር የሚያስፈጽም የሂሣብ አጣሪ (Liquidator) ቀጥሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች (ወይም ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል) መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ሠርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት የሆኑና ሕጋዊ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. ለሥራው ተገቢ ዕውቀት ያለው የሕግ ባለሙያ መመደብ የሚችሉ፣
  3. ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  4. በሂሣብ አጣሪነት ሥራ ልምድ ያላቸው፡፡

ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን በኋላ ባሉት አሥር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

አድራሻችን፡ ዥማር ሁለገብ ኢንዱስትሪ .

ባምፒስ አጠገብ አፈወርቅ ሕንፃ 1 ፎቅ፣

. 0935-98 60 07 ወይም 011-5-570767

ማሳሰቢያ፡ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡