በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽህፈት እቃ፤ ኣላቂ የጽዳት እቃ፤ የህክምና መድኃኒቶችና መገልገያ መሳሪያዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የህትመት ሥራ ውጤቶች፤ የሽንት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት የተለያዩ የጥገና (ሜንቴናንስ) አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና መለዋወጫዎች፣ የትራንስፖርት እና የጉልበት ስራ፣ የተለያዩ የፓርቲሽን እና የፍሳሽ ዝርጋታ ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽህፈት እቃ፤ ኣላቂ የጽዳት እቃ፤ የህክምና መድኃኒቶችና መገልገያ መሳሪያዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የህትመት ሥራ ውጤቶች፤ የሽንት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት የተለያዩ የጥገና (ሜንቴናንስ) አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና መለዋወጫዎች፣ የትራንስፖርት እና የጉልበት ስራ፣ የተለያዩ የፓርቲሽን እና የፍሳሽ ዝርጋታ ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 

የግዥ መለያ ቁጥር 002/2012 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ

 • ሎት 1. የደንብ ልብስ፤
 • ሎት 2. አላቂ የጽህፈት እቃ፤
 • ሎት 3 ኣላቂ የጽዳት እቃ፤
 • ሎት 4 የህክምና መድኃኒቶችና መገልገያ መሳሪያዎች፤
 • ሎት 5 ቋሚ እቃዎች፤
 • ሎት 6.የህትመት ሥራ ውጤቶች፤
 • ሎት7.የሽንት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት
 • ሎት 8. የተለያዩ የጥገና (ሜንቴናንስ) አገልግሎት
 • ሎት 9. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና መለዋወጫዎች
 • ሎት 10 የትራንስፖርት እና የጉልበት ስራ
 • ሎት 11 የተለያዩ የፓርቲሽን እና የፍሳሽ ዝርጋታ ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባችሁ መስፈርቶች፡

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው የሚቀርብ ማስረጃ 

2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ሲፒኦ ሎት1 የደንብ ልብስ፤ እና የልብስ ስፌት፤ 2,500(ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሎት2.አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 2,500(ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)፤ ሎት3 አላቂ የጽዳት እቃዎች 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)፤ ሎት4 የህክምና መድኃኒቶች እና መገልገያ መሳሪያዎች ፤ 5000(አምስት ሺህ ብር) ሎት5. ቋሚ እቃዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር) ሎት 6. የህትመት ሥራ ውጤቶች፤ 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሎት 7፤ የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎት 2,000.00(ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ሎት 8. የተለያዩ የጥገና  አገልግሎት ብር 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሎት 9. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና መለዋወጫዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር) ሎት10 የትራንስፖርት እና የጉልበት ስራ ብር 1,000(አንድ ሺህ)ሎት 11 የተለያዩ የፓርቲሽን እና የፍሳሽ ዝርጋታ ስራዎች (5,000 /አምስት ሺህ/እንዲሁም ተጫራቾች 2 እና ከ2 በላይ የጨረታ ሰነድ (ሎት) የሚገዙ ከሆነ ብር 7,000 በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ(CPO) በፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ስም ከጨረታ ሠነዱ ጋር አብሮ ማስገባት አለባቸው፡፡ 

5. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) በየሎቱ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 414 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡ 

6. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒዮ በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 

7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡ 

8. ተጫራቾች የዶኩመንታቸውን ዋናውንና ፎቶኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 

9. ተጫራች ያሸነፉበትን ዋጋ በተነገራቸው ቀን ቀርበው ውላቸውን በመፈፀም የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒዮ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡ 

10. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::ካልተጠቀሰ እንደተጠቀሰ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ 

11. የጨረታው ሳጥን የሚዘጋው ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ይዘጋል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በስራ ቀን በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ 

12. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈረመበት በ15 ቀን ውስጥ እቃውን ያቀርባል ጥገናውን እና አገልግሎቱን ይሰጣል። 

13. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ 

14. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፡- አ/ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ወረዳ 06 መሄጃ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ 

ስልክ ቁጥር፡011-8959478 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 6 ፈለገ መሰስ ጤና ጣቢያ