ሪች ኢትዮጵያ/REACH Ethiopia/ የድርጅቱን ሂሳብ በ IPSAS ማሠራት ስለሚፈልግ ይህንኑ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም አማካሪዎችን Consultants/ አወዳድሮ ለማሠራት ወይም አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል፡፡

ሪች ኢትዮጵያ/REACH Ethiopia/ የድርጅቱን ሂሳብ በ IPSAS ማሠራት ስለሚፈልግ ይህንኑ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም አማካሪዎችን consultants/ አወዳድሮ ለማሠራት ወይም አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል፡፡

ማስታወቂያ 

ድርጅታችን ሪች ኢትዮጵያ/REACH Ethiopia/ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 847/2006 IFRS እና IPSAS የተባሉ ዓለም አቀፍ የሂሳብ አሠራሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ በደነገገው መሠረት የድርጅቱን ሂሳብ በIPSAS ማሠራት ስለሚፈልግ ይህንኑ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም አማካሪዎችን consulants/ አወዳድሮ ለማሠራት ወይም አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል፡፡ 

ስስዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሥፈርቶችን፡

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው 
  • የዘመኑን ግብር የከፈለ
  • የታደሰና በዋና ኦዲተር የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫና በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድለመመዝገቡ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  • በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ኦዲት የማድረግና የIPSAS አገልግሎት የመስጠት /IPSAS Conversion Service/ፈቃድ የተሰጠው ወይም ይህንን አገልግሎት ለመስጠት የተመዘገበ 
  • የግብር ከፋይ መለያTIN#/ ቁጥር ያለው
  • ሥራውን በአጭር ጊዜ አጠናቅቆ ማስረከብ የሚችል
  • በዚህ ዝርዝር ያልተጠቀሱና ሙያውና አዋጁ የሚጠይቃቸውን ሌሎች መሥፈርቶች ሁሉ የምታሟሉ አማካሪ ድርጅቶች የምትሠሩበትን ዋጋ በዝርዝር ሁኔታና ሥራው የሚጠናቀቅበትን ቀን በመጥቀስ የመወዳደሪያ ሰነዶቻችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት (7) የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች ባለው አድራሻ በመላክ ወይም በአካል በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 

አድራሻ፡-ሐዋሳ ቤተሰብ መምሪያ ፊት ለፊት 

ስልክ ቁጥር፡ +251911718252ወይም+251916872987 

ፖ.ሳ ቁ.303 ሪች ኢትዮጵያ