< Back
በየአራዳ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ቅ/ጽ/ቤት ለሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሃና ማርያም ፉሪ ሳይት ጠዋትና ማታ ሰራተኛን የማመላለስ አገልግሎት የሚሰጥ ብዛት 1 ሚኒባስ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 012/2012
በየአራዳ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ቅ/ጽ/ቤት ለሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሃና ማርያም ፉሪ ሳይት ጠዋትና ማታ ሰራተኛን የማመላለስ አገልግሎት የሚሰጥ ብዛት 1 ሚኒባስ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በጽ/ቤታችን የከፍያና ሂሳብ ደ/የስራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚቀርበው መኪና ለስራ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነዳጅ ቅባት የሾፌር የደመወዝ፣ ጥገና እና ፅዳት ወዘተ… ወጪዎችን አቅራቢው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- የመጫን አቅሙ 11 ሰው መጫን የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ለአገልግሎት የተመደበው መኪና ሲበላሽ በምትኩም ለድርጅቱ ሌላ ተለዋጭ መኪና በወቅቱ ይመደባል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በመስኩ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፡ የዘመኑን የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የTIN No ሰርተፍኬት፣ ሊብሬ እና የሶስተኛ ወገን ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 2,500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ በተጠቀሰው መመሪያመሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ መሙላትና በታሸገ ኤንቨሎኘ ኦርጅናልና ኮፒውን በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በስራ ሰዓት በዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የመክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ጀምሮ የውል ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም ሲፒኦ የአፈፃፀም ዋስትና ማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ፡-ቁጥር 0118-27-58-07/0913-04-74/12/0913281962 ደውለው መጠየቅ ወይም ሃና ፍሪ ሳይት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ወረድ ብሎ ኮብልስቶን መፍለጫ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ኮንዶሚኒየም ግንባታ ሳይት ውስጥ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 1 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአ/አ/ከ/አስ/ቤቶች ልማትና አስተዳደር
ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የአራዳ ቤቶች ልማት ቅ/ጽ/ቤት