< Back
የፍቼ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ ባለ G+3 ሕንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የፍቼ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ ባለ G+3 ሕንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ፡
1 በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
2. ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው ተቋራጮች የሆኑ፡፡
3 የብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺ) CPO በመ/ቤቱ ስም በማሰራት ከፍቼ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ዝርዝር የጨረታውን መመሪያ ከተዘጋጀው ሰነድ ላይ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት መወዳደር ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011135 10 11 ወይም 011135 17 28 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፍቼ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት