ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሴፍትኔት እና ከተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክስተት ጋር በተያያዘ ከመጋዘን ወደ መጋዘን እና በዘጠኙም ክልሎች ለሚገኙ ነባርና አዲስ ወረዳ ጣቢያዎች የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ፍሬም ወርክ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል

Tender
< Back

ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሴፍትኔት እና ከተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክስተት ጋር በተያያዘ ከመጋዘን ወደ መጋዘን እና በዘጠኙም ክልሎች ለሚገኙ ነባርና አዲስ ወረዳ ጣቢያዎች የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ፍሬም ወርክ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሴፍትኔት እና ከተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክስተት ጋር በተያያዘ ከመጋዘን ወደ መጋዘን እና በዘጠኙም ክልሎች ለሚገኙ ነባርና አዲስ ወረዳ ጣቢያዎች የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ፍሬም ወርክ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 1. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ማስታወቂያ ጥሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየክልሎች የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በጥሬ ገንዘብ የማይመለስ ብር በመክፈል ንፋስ ስልክ በሚገኘው በጀትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
 2. ጨረታው ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሲሆን፣ ስርዓቱም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ እና መመሪያ መሠረት ነው፡፡
 3. የጨረታ ማስረከቢያ ቦታ ደንበል ሲቲ ሴንተር ፊትለፊት በሚገኘው ቢተወደድ ባህሩ ህንጻ ከሚገኘው ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የገበያ ጥናትና አቅርቦት ቡድን 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 52 በተዘጋጀው ሳጥን በወቅቱ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 4. ተጫራቶች በየክልሎች ያሉትን ወረዳዎች የዋጋ እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት እና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላና ሐረር እስከ 13/08/2012 . 400 ታሽጎ 430 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል እንዲሁም ደቡብ፣ በቤሻንጉል፣ አማራ፣ ትግራይ፣ አፋር እና ከማ/መጋዘን ወደ ሌላ መጋዘን በ14/8/2012 ዓም 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል፡፡
 5.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ በየክልሎች የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም ዉል ሲዋዋሉ 10% ለአሸነፉበት ቦታ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ/ ሰነድ/ የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ በየከልሎች በሚገኙ ወረዳዎች ጣቢያዎች በቀረበው ዝርዝር መሰረት በግልጽ በሚነበብ ጽሁፍ ተሞልቶ መቅረብ አለበት ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
 7. ተጫራቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማሟላት አለባቸው፡፡ ይህንን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
 • በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ 2012 . የንግድ ሚኒስቴር ንግድ ፈቃድና ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
 • የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ ታክስ ክሊራንስ/
 • የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፍኬት ወይም በሰፕላየር ሊስት በዌብ ሳይት፣ እንዲሁም የተሽከርካሪዎች ዝርዝር፣ የሰሌዳ ቁጥር የመኪናው አይነትና የመጫን አቅም የተመለከተ መረጃ ከትራንስፖርት ባለስልጣን ወቅታዊ መረጃ እና የታደሰ ፈቃድ እና አስፈላጊ ሰነዶችን በሙሉ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች ዝቅተኛ የመጫን አቅም ለሶማሌ ክልል 3,000 / እና ለሌሎች ክልሎች 4000 / በላይ ሊጭኑ የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ ይኖርበታል፣

8. እያንዳንዱ ተጫራች ዋጋ የሚሰጠው ለማደያ ጣቢያ ሳይሆን ወረዳን መሰረት ያደረገ ሆኖ በወረዳው ውስጥ የሚገኝ አንድ እና ከአንድ በላይ ማደያ ጣቢያዎች ሊኖረው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ሁሉንም ጣቢያዎችን የሚሸፍን መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፣

9. ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ቅጽ 02 የትራንስፖርት ድርጅቱን የተመለከተ ጠቅላላ መረጃ ቅጽ 01 በትክክል ተሞልቶና ማህተም ተደርጎ ከሰነዱ ጋር በሚመለከተው ሃላፊ ተፈርሞና ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11.የበለጠ መረጃ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-5 58 43 31/29 መጠየ ይችላሉ፡፡

 

ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

አዲስ አበባ