የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተቋሙ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ኮምፒዩተር ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒና የተለያዩ የቢሮ ውስጥ የመገልገያ ማሽኖችን ብቃት ያላቸው የቢሮ መገልገያ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ እና የተለያዩ ማሽኖችን ጥገና የሚሰሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል

Tender
< Back

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተቋሙ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ኮምፒዩተር ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒና የተለያዩ የቢሮ ውስጥ የመገልገያ ማሽኖችን ብቃት ያላቸው የቢሮ መገልገያ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ እና የተለያዩ ማሽኖችን ጥገና የሚሰሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ መለያ ቁጥር 

ኢ.ኮ. ዲ.ሱ.ሥ.ኮ/13/2012 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተቋሙ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ

  • ኮምፒዩተር ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒና የተለያዩ የቢሮ ውስጥ የመገልገያ ማሽኖችን ብቃት ያላቸው የቢሮ መገልገያ ኮምፒዩተር፣
  • ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ እና የተለያዩ ማሽኖችን ጥገና የሚሰሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል። 

በዚሁ መሠረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። 

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ወይም ቲኦቲ (TOT) ከፋይ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ማቅረብ የሚችሉ እና የሙያ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። 
  2. ተጫራቾች በቂ የጥገና አገልግሎት የሚሰጡበት ቦታ እና በሰው ኃይል የተደራጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡ 
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  5. ጨረታው ሚያዝያ 29 ቀን 2012ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡ 
  6. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ብር 10,000.00 በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል::  
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው:: 
  8. ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሕንፃ 1 አራተኛ ፎቅ፣ በኮርፖሬት አገልግሎቶች የግዥ ቡድን ቢሮ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ሕንፃ ፊት ለፊት ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ 

ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 

ስልክ ቁጥር፡- +251 118720722 

አዲስ አበባ 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን 

ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች 

ኮርፖሬሽን