የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀዋሳ፤ በአዳማ፤ በቢሾፍቱ እና በአዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ ለሚያደርጋቸው የተለያዩ ሥልጠናዎች፤ ኮንፈረንሶች፤ ዎርክሾፖች እና ስብሰባዎች በውል ለሁለት ዓመት ፀንቶ የሚቆይ የሆቴል አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀዋሳ፤ በአዳማ፤ በቢሾፍቱ እና በአዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ ለሚያደርጋቸው የተለያዩ ሥልጠናዎች፤ ኮንፈረንሶች፤ ዎርክሾፖች እና ስብሰባዎች በውል ለሁለት ዓመት ፀንቶ የሚቆይ የሆቴል አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ለ2 ዓመት የሚቆይ የሆቴል አገልግሎት 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታው መለያ ቁጥር፡ብግጨ/ኢሕጤኢ/ግኬቲ/ሆ/አ/049/2012 

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀዋሳ፤ በአዳማ፤ በቢሾፍቱ እና በአዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ ለሚያደርጋቸው የተለያዩ ሥልጠናዎች፤ ኮንፈረንሶች፤ ዎርክሾፖች እና ስብሰባዎች በውል ለሁለት ዓመት ፀንቶ የሚቆይ የሆቴል አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም፡– በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟልት ይጠበቅባቸዋል፡ 

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ ቫት ሰርተፍኬት፤ የቲን ቁጥር ሰርተፍኬት፤ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Public Procurement Property Administration Agency PPPAA፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ (ታክስ ክሊራንስ)፤ በአዲስ አበባ ከኢንስቲትዩቱ 5 ኪሜትር በላይ ርቀት የሌላቸው ሆኖ የኮከብ ደረጃቸው 3 እና ከዚያ በላይ፤ በሀዋሳ አራት ኮከብ፤ በቢሾፍቱ እና አዳማ 3 እና ከዚያ በላይ የኮከብ ደረጃ ያላቸው፤ የሆቴል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፤ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 7፡30 ሰዓት ከግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ዶክመንት ብቻ የሚከፈት ሲሆን የፋይናሽያል ዶክመንት የቴክኒካል ግምገማ ከተከናወነ በኃላ በደብዳቤ በማሳወቅ ይከፈታል፡፡ 
  4. የጨረታው የቴክኒካል መክፈቻ 15ኛው ተከታታይ ቀን በመንግስታዊ በዓላት/በህዝባዊ በዓላት/ቅዳሜ/እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው ሰዓት ይዘጋል/ይከፈታል፡፡ 
  5. ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-277-10-54/56 መደወል ይችላሉ 
  • አድራሻ፡- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ 

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

አዲስ አበባ