የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2012 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ግንባታ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ጥገና የመኖሪያ ካምፕ፣ አዳራሽ፣ ቢሮዎችና ዐ1 ማማ ሰርቶ የሚያስረከብ፣የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እንዲሁም የተለያዩ የመኪናዎች የሙቀት መከላከያ እና የወንበር ልብስ የሚያቀርብ፣ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ መኪና ኪራይ የሚያቀርብ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚያቀርብ፣

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2012 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ግንባታ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ጥገና የመኖሪያ ካምፕ፣ አዳራሽ፣ ቢሮዎችና ዐ1 ማማ ሰርቶ የሚያስረከብ፣የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እንዲሁም የተለያዩ የመኪናዎች የሙቀት መከላከያ እና የወንበር ልብስ የሚያቀርብ፣ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ መኪና ኪራይ የሚያቀርብ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚያቀርብ፣

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 

002/2012 

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2012 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

በመሆኑም፡-

 1. የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ 
 2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ 
 3. የተለያዩ የኮንስትራከሽን ግንባታ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና የቧንቧ ዕቃዎች፣ 
 4. የተለያዩ ጥገና የመኖሪያ ካምፕ፣ አዳራሽ፣ ቢሮዎችና ዐ1 ማማ ሰርቶ የሚያስረከብ፣
 5. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እንዲሁም የተለያዩ የመኪናዎች የሙቀት መከላከያ እና የወንበር ልብስ የሚያቀርብ፣ 
 6. የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ መኪና ኪራይ የሚያቀርብ፣ 
 7. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚያቀርብ፣ 
 8. የሚጫረቱበት የዕቃ ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግዥ ማስተባበሪያ ክፍል ቢሮ ቁጥር 19 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ። 
 9. የሚጫረቱበትን የዕቃ ዋጋ የሚገልፅ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስገብቶ ይታሸጋል። 
 10. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስከ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው። 
 11. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና ከጨረታ መክፈቻ ቀናት አስቀድመው ማቅረብ ለሚችሉባቸው ዕቃዎች አንዳንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 12. ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 13. ተጫራቾች የተለያዩ ጥገና የመኖሪያ ካምፕ፣ አዳራሽ፣ ቢሮዎችና 01 ማማ ሰርቶ ለማቅረብ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፤ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እንዲሁም የተለያዩ የመኪናዎች የሙቀት መከላከያ እና የወንበር ልብስ የሚያቀርብ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር፣ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ግንባታ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና የቧንቧ ዕቃዎች ለማቅረብ ብር 5.000.00 (አምስት ሺህ ብር )፣ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ብር 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)፤ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች ብር 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)፣የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ መኪና ኪራይ ብር 2.000.00 (ሁለት ሺህ ብር ) የተለያዩ የደንብ አልባሳት ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 
 14. በጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግቤት የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡ 
 15. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በሲፒአ (CPO)ብቻ በማስያዝ ውል መግባት ይኖርበታል፡፡ 
 16. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀናት ከሞላው በዚያው ዕለት በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ታሽጎ 7፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም በዓል ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ይከፈታል፡፡ 
 17. አማራጭ ዋጋ ሆነ አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታማቅረብ አይቻልም። 
 18. መስሪያ ቤቱ በግዥ ወቅት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 19.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ 
 20. የበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥሮች ፡- 0911 99 77 74/0111 57 91 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን 

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ