በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሣኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማና የተለያዩ መገልገያ፤ የክበብ ጨረታ፣ የህፃናት እቃዎች የሚሆኑ ዝርዝር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር መ/ኩ/ምዝገባ ኤጀንሲ ግ/ጨ/06/201

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሣኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የተለያዩ ዕቃዎችን እነሱም፡-

 • የደንብ ልብስ፣
 • የፅዳት ዕቃዎች፣
 • የፅህፈት መሳሪያዎች፣
 •  ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
 • የተሽከርካሪ ጎማና የተለያዩ መገልገያ፤
 • የክበብ ጨረታ፣ የህፃናት እቃዎች የሚሆኑ ዝርዝር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ፡

 1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የታደሰና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ለዕቃ አቅራቢነት የሰጠውን ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣታትሞ ከወጣበት 18/7/2012 ዓ/ም ድረስ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመ/ቤታችን ክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣ 
 3. የጨረታውን ሰነዶች ዋጋ የሰጠበትን ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም መስሪያ ቤታችን በሚያዘጋጀው የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ መሰረት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በድምሩ በአራት ፖስታ ለየብቻ ታሽጐ ባዘጋጀነው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡ 
 4. ጨረታው 2/8/2012 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በመ/ቤቱ ሚኒ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 
 5. . ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን የተጠየቀበት ማቅረብ አለበት፡፡ ለማቅረብ አስቸጋሪ የሆኑትን ዕቃዎች በአካል ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 6. በጨረታው አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ መ/ቤቱ  የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡ 
 7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሆሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
 8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 9. . ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ስልሳ የስራ ቀናት ነው፡፡ 
 10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ማሳሰቢያ፣ 

የዕቃው ዝርዝር ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በተዘጋጀው የዕቃ ዝርዝር መሰረት በእያንዳንዱ ተራ ቁጥር የምታቀርቡበትን የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጭምር እንዲገለጽ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ፍላሽ ይዘው በመምጣት በሶፍት ኮፒ እንዲወስዱ እናሳስባለን፡፡ 

አድራሻችን፡- አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ 

ስልክ ቁጥር፡- 011-56-78-32 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ