የቦሌ ገርጂ የመ/ደ/ት/ ቤት የግንባታ ጥገና ስራዎች በመደበኛ በጀት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ግልፅ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ 

የቦሌ ገርጂ የመ/ደ/ት/ቤት የግንባታ ጥገና ስራዎች በቀን 26/6/2012 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማውጣቱ ይታወቃል። ነገር ግን ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ስለነበረ አሁን ግን የቦሌ ገርጂ የመ/ደ/ት/ ቤት የግንባታ ጥገና ስራዎች በመደበኛ በጀት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። 

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው። 
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  • በግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገበ።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 3000 /ሦስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ በደረጃ 8።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ማቅረቢያ ሰነድ በስራ ሰዓት ከመስሪያ ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 18 የማይመለስ 100 ብር በመግዛት በጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በታሸገ ሁለት ኤንቨሎፕ ማሰታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ከ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት በ8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በትምህርት ቤቱ ቤተ መጽሐፍት ይከፈታል። 

መስሪያ ቤቱ የተሻስ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

አድራሻ፦ ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት ገባ ብሱ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ፡፡ 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 629 07 81/ 011 629 05 76 

በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 13 ት/ጽ/ቤት 

 የቦሌ ገርጂ የመ/ደ/ት/ ቤት