የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር ልክ/ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት/ 02/12 የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር ልክ/ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት/ 02/12

 • የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎችን
 • ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
 • የፅዳት እቃዎችን፣ 
 • የደንብ ልብሶችና
 • ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።  
 1.  በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። 
 2. ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም 2012 ዓ.ም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
 3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአጠቃላይ የእቃዎች ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው። 
 4. ተጫራቾች የጨታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመቶ ብር/ በመክፈል ማስታቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። 
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸው እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብላቸው እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት። 
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በማድረግ ማስታቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 31 ማስገባት አለባቸው። 
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት። ካላካተተ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል። 
 8. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 31 ይከፈታል። እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። 
 9. ወረዳው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው። 

አድራሻ፡- አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ ባስው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከል ነው። 

የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 011 869 37 13/ 011 869 54 40/ 011 859 11 17 

በልደታ ክፍስ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር 

ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት