በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለገጣፎ ለገዳዲ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የህትመት ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለገጣፎ ለገዳዲ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የህትመት ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለገጣፎ ለገዳዲ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የህትመት ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 

 1.  ህጋዊ የንግድ ስራ ምዝገባ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (ማስረጃ ማቅረብ) ይኖርባቸዋል፡፡
 2. የቫት ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ ሠርተፊኬት ያላቸው፡፡ 
 3. ከፌዴራል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚ/ር ወይም ከክልሎች ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በአቅራቢነት ተመዝግበው ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ 
 4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም ::
 5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ጽ/ቤቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብና በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 6. ጨረታውን ለመግዛት ለያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በለገጣፎ ለገዳዲ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000061739274 ገቢ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 5 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
 7. ማንኛውም ተጫራች በእያንዳንዱ ለሚጫረትበት ሰነድ ላይ በሚታይ የድርጅቱ ማህተም መምታት አለበት : 
 8. በጨረታው የተሸነፉት ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
 9. የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ በታሸገ ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ 
 10. ማንኛውም ተጫራቾች በሚጫረቱበት ዘርፍ ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ቀን የእቃውን ናሙና ማቅረብ አለባቸው። .
 11. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውለን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውሉ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤታችን ገቢ ይሆናል፡፡ 
 • ጨረታውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
 • የጨረታው ሰነድ የሚሸጥ ጋዜጣ ካወጣበት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5ውስጥ ሲሆን በጨረታው የሚገባው በ16ኛው የሥራ ቀን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከ2፡30-4፡30 ሰዓት ሆኖ በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን በ5:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 
 •  ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ድራሻ፡- በደሴ መስመር ከመገናኛ 12ኪሜ ርቀት ላይ ልዩ ስሙ ሚሽን ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡ 

የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት