ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ ገ/2ኛ/ደ/002/2012
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2012 ዓ.ም በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የእቃ አይነት በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- Lot 1. የጥገና ዕቃዎች፣
- Lot 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- Lot 3 ቋሚ ዕቃዎች፣
- Lot 4 የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣
- Lot 5. የፅዳት ዕቃዎች፣
- Lot 6. ኬሚካሎች እና የትምህርት ዕቃዎች፣
- Lot 7. የደንብ ልብስ፣
- Lot 8. የህክምና ዕቃዎች፣
- Lot 9. ግቢ ማስዋብ እና የፓርትሽን ስራዎች፣
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኦርጅናልና ኮፒ
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
- ተጫራቶች ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ኦርጅናልና ኮፒ
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5% በጥሬ ገንዘብ፣ በCPO ለእያንዳንዱ Lot ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 4፣ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ናሙና (በፎቶ የሚቀርቡትንም እና በእቃ የሚቀርቡትን) ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናቶች ከቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 4፡30 በቢሮ ቁጥር 4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል የጨረታው ቀን እሁድ ወይምቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የመጀመሪያው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ማህተም በማድረግና አስፈላጊ ሰነዶች በማሟላት በሁለት ኤንቨሎፕ ኮፒ እና ኦርጅናል ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ ካላቸው በስልክ ቁጥር፡- 0118886850 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ በራሳቸው ወጪ ለገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት