በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ ተዛማች፤ የጽህፈት መሳሪያዎች ቋሚ ዕቃዎች የጽዳት ዕቃዎች ፤ የሰራተኞች የደንብ ልብስና ስፌት (የተሰፋ ሳምፕል ማቅረብ የሚችል) ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር፣-አ/ከ/ክ/ከ/ መ/5/ፋ/ጽ/002/12 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስስሆነም:)

 • ሎት 1 የቢሮ አላቂ ተዛማች የጽህፈት መሳሪያዎች 
 • ሎት 2 ቋሚ ዕቃዎች 
 • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች 
 • ሎት 4 የሰራተኞች የደንብ ልብስና ስፌት (የተሰፋ ሳምፕል ማቅረብ የሚችል) 

በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ 

 • በጨረታው ለመካፈል የንግድ ምዝገባ ፤ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና በፌደራል ግዥ ንብረት አስተዳደር ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 
 • ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ክሪላንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ለጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond ) በየሎቱ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ (cpo) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለእያንዳንዱ በየሎቱ የተጠመሩትን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/በመክፈል ከግዥና ንብረት ቡድን ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቀደም ሲል ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
 • ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሲያስገቡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መሆን ይኖርበታል። ስሌት ሲሰላ ስህተት ሲኖረው መ/ቤቱ የሚወስደው ነጠላ ዋጋውን ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስገቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡ አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡ –
 • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሠነዳቸውን ሲያስገቡ በሰነዱ ላይ ተፈርሞበት እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት መሆን ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሊያስገቡ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦርጅናል እና ፋይናንሻልና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማዘጋጀት ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት እና በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ –
 • የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% /አስር በመቶ/cpo/ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
 • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ በሰነዱ ላይ
 • ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር/የስራ ቀናት/ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 1፡30 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጧቱ 4፡ 30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት አ/ከ/ክ/ከ/ወ/5/ፋ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት ክፍል ይከፈታል፡፡ 

መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ . 

አድራሻ፡- ከመድሓኒዓለም ት/ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡ 

ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 0118 279560 

ማሳሰቢያ:- በተጫረታችሁበት ዕቃ ላይ ዋጋ ስታስገቡ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ መወዳደር የሚቻለው ንግድ ፍቃዱ ላይ በተሰጠው ስራ ዘርፍ ብቻ ነው ያስገባችሁት ሳንፕል ዕቃዎች ላሸናፊው ከተገለፀ በኋላ ባሉት 60 የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡ ባትወስዱ ግን ለሚፈጠረው ክፍተት ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት