በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ ለ202 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ማለትም አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ህትመቶች፣ የህክምና መገልገያ መሳርያዎች እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ 

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ ለ202 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ማለትም

 • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
 • ቋሚ ዕቃ፣ 
 • የፅዳት ዕቃ፣
 • የደንብ ልብስ፣
 • ህትመቶች፣
 • የህክምና መገልገያ መሳርያዎች እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል። 
 1.  ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው። 
 2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው። 
 3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። 
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
 5. ተጫራቾች የጨታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 100 /መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ረዳትፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮቁጥር 35 ቀርቦ መግዛት ይችላሉ። 
 6. ተጫራቾች በሙያቸው ብቃት ማረጋገጫ እና የሲኦሲ መመዘኛ የሚጠይቅ ከሆነ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በማሸግ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። 
 8. ጨረታው በ10ኛውቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣይቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በጤና ጣቢያው ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 35 ይሆናል። 
 9.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም። 
 10. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

አድራሻ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ 

በስልክ ቁጥር 011 470 82 52/07 440 36 78/011 440 62 61 

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ 

የወረዳ 9 ጤና ጣቢያ