የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር 08/2012
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የኦሮሚያ የገጠር ልማት ሴክተር ጽ/ቤት የሆኑ የተለያዩ ንብረቶች( ደፕ/DAP/፤ ዩሪያ/UREA እና የእርሻ መሳሪያዎች/BBM) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 13 /2012 ዓ.ም፤ ድረስ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- የኤጀንሲው አድራሻ ፤ አዲስ አበባ ሳርቤት ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስድ መንገድ ጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ሳይደርስ ቤተልሔም ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት ብቻ ነው::
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሚያዚያ 13 /2012 ዓ/ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከ3፡00-11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 14/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዚያ 14/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-23-68-19 ወይም 011-1-22-25-24 ወይም 011-1-23-68-22 በመደወል ወይም የጨረታ ሠነዱን በማንበብ መረዳት ይቻላል፤ CPO ለማሰራት)
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት የመንግት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ/
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ/ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ