የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ቋሚና አላቂ እቃዎች የስፖርት ትጥቆች የህትመት አገልግሎት ሬዲ ሜድ ምንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር – አ/አፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ቢሮ ግ/ጨ/ቁ/05/2012 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል :: 

  • ሎት 1ቋሚና አላቂ እቃዎች
  • ሎት 2፡የስፖርት ትጥቆች
  • ሎት 3፡የህትመት አገልግሎት
  • ሎት 4 ሬድ ሜድ ምንጣፍ 

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ  ተጫራቾች 

  • ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ 
  • ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑ የመንግስት ግብር የተከፈለ መረጃ 
  • የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው 
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስፖርት ኮሚሽን ህንፃ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ 10ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ ቢሮ ቁጥር
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 

ለሎት1 ቋሚና አላቂ እቃዎች 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር / 

ለሎት 2 የስፖርት ትጥቆች 5000.00 /አምስት ሺህ ብር / 

ለሎት 3 የህትመት አገልግሎት 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር / 

ለሎት 4 ሬድ ሜድ ምንጣፍ 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር / 

በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦማስያዝ ይኖርባቸዋል 

4.ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ የጨረታ ቁጥርና የእቃው አይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት አለባቸው :: 

5. ጨረታው በአዲስ ዘመን በወጣ 11ኛው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በ4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል :: 

6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ናሙና የሚያስፈልገው የእቃ አይነት ከሆነ ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው :: ናሙና ለማይቀርብባቸው የእቃው ዓይነት በሚቀርበው እስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል :: 

7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ስፖርት ኮሚሽን 10ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር፡- 0118120635  አዲስ አበባ 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና  የሰው ሃብት ልማት ቢሮ …