የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ የአካል ጉዳተኞች ማበልጸጊያ ማዕከል ግንባታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
- ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዛ በላይ የሆነ፣
- ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያወጡና ለ2012 ዓ.ም ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክሜንት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከቢሮው የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 140,000 /አንድ መቶ አርባ ሺህ ብር/ከቴክኒካል ኦርጅናል ሠነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራቀን ይሆናል።
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 28/2010 እና በመመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሠርኩለር ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 046-220-11-70/046 220 97-97/046 220 31 68/ 046-221-13-56
የደቡብ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ሀዋሣ፣