የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮምፒዩውተር መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

ኮልፌ ቀራኒዮ /ከተማ የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት

 • ሎት 1. ኮምፒዩውተር

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል::

 1. ከላይ በሎት በተጠቀሰው ዕቃዎች አግባብነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የጨረታ የምስክር ወረቀት ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት / ወይም በዕቃ አቅራቢዎች የምስክር ወረቀት ያለው የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 2. ተጫራቶች በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ወይራ ሰፈር ወደ ቤተል መውጫ በስተግራ የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመገኘት የማይመለስ 50.00/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል በዘርፉ ለመሰማራታቸው የሚገልፅ ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣ እስከ 10ኛው ቀን 1100 ሰዓት ድረስ ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ 2,110.00 /ሁለት አንድ መቶ አስር ብር/በየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት ስም ሲፒኦ በማዘጋጀት ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ በመግለፅ መሉ አድራሻቸውን ///ከተማ ወረዳ 06 የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
 6. የጨረታ ሰነድ የገዙትን ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች አንዱ በሠጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
 9. /ቤቱ ለግዥው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ጥብቅ ማሳሰቢያ፡ከሎት1 የተጠቀሱት ዝርዝሮች እንደተጠበቁ ሆኖ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ስፔስፊኬሽን ማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113696814

አድራሻ፡በኮልፌ ቀራኒዮ /ከተማ ወረዳ 06 የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት

የኮልፌ ቀራኒዮ /ከተማ የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ /ቤት