በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ስር የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2012 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ የሚያስፈልገውን አላቂ እና ቋሚ የትምህርት እቃዎች እንዲሁም የፅዳት እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክሶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ /ከተማ ወረዳ 10 ስር የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት 2012 . ለትምህርት ቤቱ የሚያስፈልገውን

 • አላቂ እና ቋሚ የትምህርት እቃዎች እንዲሁም
 • የፅዳት እቃዎች እና
 • ኤሌክትሮኒክሶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡

 1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 2. የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃ እና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ
 3. ከግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት አይነት የማይመለስ ብር 30(ሰላሳ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በየካ /ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO ብር 3000(ሶስት ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
 6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በሚገባ በታሸገ እና ማህተም ባረፈበት ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ የሚወዳደሩበት ዋጋ በተዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
 7. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ተጫራቾች በጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በሙሉ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ ወዲያው 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
 10. መስሪያ ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡የካ /ከተማ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 02 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ህዝብ ደህንነት በሚያወጣው አስፓልት ከፍ ብሎ ወረዳ 10 አጠገብ ሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116460189 ወይም ወረዳ 10 ሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በግንባር በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር /ቢሮ በየካ /ከተማ ወረዳ 10

የሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት