የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም ከህብረተሰብ ተሳትፎ በተሰበሰበው በጀት በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አማካኝነት በወረዳ ውስጥ ላሉት ሚሊሲያ (የአካባቢ ጥበቃ መከላከያ) ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ስለመሳተፍ የሚችሉ የንግድ የሥራ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቶች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዳሞት ጥላሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 16 አንድ መቶ ብር (ብር 100) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች ዕቃውን እስከ አጫራች መስሪያ ቤት ድረስ አምጥቶ ለማስረከብ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና የኦርጅናሉ አንድ (7) ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በማንኛውም ባንክ የተመሰከረለት CPO በኦርጅናል ሠነድ ውስጥ ታሽጎ ማቅረብ የሚችል ::
- በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15( እሥራ አምስት) በተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በዳ/ጉ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት በነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበቡና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
- ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ተጫራቾች
- የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ እና ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-046 893 25 10 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በወላይታ
ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስና
ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት