በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የአካባቢ ጥበቃ፣ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን የደንብ ልብስ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ለሁተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 

034/2012 የደንብ ልብስ ግዥ 

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የአካባቢ ጥበቃ፣ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን የደንብ ልብስ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም 

.

የዕቃው ዓይነት

መለኪያው

ብዛት

ምርመራ

1

የደንብ ልብስ ግዥ

በቁጥር

 

ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል

  • ተጫራቶች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እና ሌሎች ያሏቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልፅ ሊነበብ በሚችል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት አሮጌው መናኸሪያ አጠገብ የቀድሞው ግብርና ቢሮ፣ ቢሮ ቁጥር 7 ሀዋሳ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ :: 
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ /ፕሮፎርማ/ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒና ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 12ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ/ፋ/ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 71 በቀድሞው ግብርና ቢሮ አሮጌው መናኸሪያ አጠገብ ሀዋሳ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ :: 
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ12ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 71 በቀድሞው ግብርና ቢሮ አሮጌው መናኸሪያ አጠገብ ሀዋሳ ይከፈታል ፡፡ 
  • መ/ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን (ብዛት) ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ 
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታው ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱ ሥነ-ሥርአት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል፡፡ 

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች 

ክልል መንግስት የአካባቢ ጥበቃ፣ደንና 

የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን