የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2012 በጀት ዓመት በጨረታ ቁጥር 002/2012 ለት/ቤቱ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ
- ላሚኔተር ማሽን፣
- ፕሪንተር፣
- ኮምፒዩተር፣
- የመምህራን ማስተማሪያ ጠረጴዛና ወንበር፣
- የስፖርት መምህራን ጫማ እና ቱታ፣
- ለሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
- ለሰራተኞች ቦርሳ፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡
- የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 5000.00 ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀና ለዚህም ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ በክ/ሂ/ግ/ን/አስ እና ጠ/አገ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በክ/ሂ/ግ/ን/አስ እና ጠ/አገ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡ዐዐ ሰዓት በት/ቤቱ በክ/ሂ/ግ/ን/አስ እና ጠ/አገ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን መሉ ለመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ በወረዳ 2 ፋና ዐ2 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀሞ አንበሳ ጋራዥ ፊት ለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፡– 0113698159 /0118961899
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት