በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 በጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው ለውስጥ ውድድር አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር መከ/ዩኒ//06/2012

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ 2012 በጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው ለውስጥ ውድድር አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ሁሉም ተጫራቾች እቃዎችን ለማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ፣ የታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (ቲን) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከባለስልጣን የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚችሉ፡፡
  2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡ እና የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 23,713.00( ሃያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ አስራ ሦስት ብር)ብቻ በኢትዩጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንት (90 ቀን) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ደብረ ዘይት ቢሾፍቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ለተዘጋጀው ሰነድ ክፍያ ፈፅመው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5.  ሲፒኦ ሲዘጋጅ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በሚል ስም ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ዶክመንቶችን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፓስታ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከ17/7/2012 እስከ 7/8/2012 . በመከ/ዩኒቨርሲቲ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድና ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው 7/8/2012 . ከጠዋቱ 400 ሠዓት ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በእለቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለዚሁ በተዘጋጀ ቢሮ በግልፅ ይከፈታል፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9.  ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 -430 – 84 -19 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ቡድን ቢሾፍቱ