በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን በ2012 በጀት ዓመት በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት በተመደበ በጀት ለፕሮግራሙ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች፤ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ ፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞችን እና የጽዳት እቃዎች በአገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን 2012 በጀት ዓመት በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት በተመደበ በጀት ለፕሮግራሙ አገልግሎት የሚውሉ

 • ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች፤
 • የጽህፈት መሣሪያዎች፤
 • ፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞችን እና
 • የጽዳት እቃዎች በአገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላቸው፣
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ተመዝጋቢ የሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ 1-4 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
 6. ስለ እቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ፣
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና 1% ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
 9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ አንድ ወጥ በሆነ ፓስታ በጥንቃቄ አሽጎ ከአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ /ቤት ትልቁ አዳራሽ ፊት ለፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በእስከ 30ኛው ተከታታይ ቀን ድረስ 230 ሰዓት እስከ 1130 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 10. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ እስከ 30 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ 31ኛው ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ 430 ሰዓት ፍላጎት ያላቸው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ///////ቤት ትልቁ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3 ሰዓት ተዘግቶ 330 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
 11. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የገዥ /ቤት አድራሻ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ባህር ዳር

ባይ ማዶ ቀበሌ 11 አዴፓ /ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 0582180014/0582181103

ፋክስ: 0582180229/0582181132

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም //ቤት