በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የግዥ ጨረታ ቁጥር መ/ቁ WGCE 

0018/2012 

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ፣

  • የግንባታ ዕቃዎች፣
  • የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ በፌዴራል መንግስት የግዥ አዋጅ ቁጥር 649/2001 መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 
  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀትና በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ኦርጅናል የድጋፍ ደብዳቤ ከሀገር ውስጥ ገቢ አስተዳደር ማቅረብ የሚችሉ፣ ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጠና የሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው ከሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለመኪና ጥገና ተወዳዳሪዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። 
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በመሙላትና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/8/2012 ዓም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ “ስሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት የግንባታ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ ጨረታ” በሚል ማስገባት ኣለባቸው ። 
  3. ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የብር 10,000.00 ( አሥር ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው ። 
  4. ጨረታው 02/08/2012 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ጽ/ቤት ነው። 
  5. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ። 

ስልክ ቁጥር: -04621100 19፣ 

ፋክስ – 046211 0025/29/13 

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶ ገነት የደንና 

የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ 

ወንዶ ገነት