የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አርማ/ሎጎ/ ዲዛይን ለማሰራት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2012

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አርማ/ሎጎ/ ዲዛይን ለመሰራት ታሳቢ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

 1. ቀላልና ቀልጣፋ /Simple/clear
 2. ሳቢና ውብ |Attractive/Appealing/
 3. በቀላሉ የሚታወስ/Recognizable/
 4. በተለያዩ ጉዳዮች መዋል የሚችል/Adaptable/ለቢሮው ድረ ገጽ አካውንት ለደብዳቤ፣ ለማህተም ሎጎ
 5. የተቋሙን ስራና ራዕይ የሚገልጽ/Expressive/ ዘመን ተሻጋሪ/Modern/Long – lasting/ የሆነ ሎጎ ለማሰራት ይፈልጋል ፡፡

በሶፍት ኮፒ እና በሀርድ ኮፒ

ስለዚህ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

 1. ተጫራች በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰው ዲዛይን ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ የያዙና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተመሰከረ 10,000.00 ብር /CPO/ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
 3. ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራሰዓት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮአችን ከግዥ ዳይሬክቶሬት 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
 4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኣሟልቶ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ብሎ በመለየት ኦርጅናል እና ኮፒዶክመንቶችን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን  ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 የስራ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 230 ሰዓት እስከ 1130 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
 5. ጨረታው 11ኛው ቀን 330 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው አዳራሽ ይከፈታል።ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣
 6. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች 7 ቀን በኋላ ይመለሳል፣
 7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ በተገለፀ 7/ሰባት/ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ግዥ ዳይሬክቶሬት መጥቶ ውል መፈረም አለበት።ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
 8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ ሎጎውን ወደ በቢሮው ስም በባለቤትነት ገቢ ማድረግ አለበት፣
 9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 122 64 56

አድራሻ፡-6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ /ቤት ፊት ለፊት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ