ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
የቁም ደን ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ የማስታወቂያ
ቁጥር OFWE I/A/B/GU 02/2012
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የኢሉባቦር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገባ ዲዴሳ፣ ገብረዲማ ዲስትሪክቶች ሥር የሚገኙትን የባህር ዛፍ ግንድ፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶ፣ የአጠና እና የባህር ዛፍ ግንድ ማገዶ እንጨት ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡
- የግንዲላና የአጠና ሽያጭ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም “TIN” number/ ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በ100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢሉባቦር ቅ/ጽ/ቤት/መቱ ቶታል ማደያ ፊት ለፊት በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና (Bin Bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 6% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሳይት ለቀረቡት የምርት ዓይነቶች በሙሉ ዋጋ የማቅረብ ግዴታ አለበት/ለተወሰነ የምርት ዓይነት ብቻ መርጦ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም እንዲሁም በአንድ ሳይት ላይ የተለያዩ የምርት ዓይነቶች የሚገኙ ከሆነ የአሻሻጥ ሁኔታ በሄክታር ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0474414196 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
የኢሉባቦር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት