ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ መለያ
ቁጥር 006/2012
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ በ2012 በጀት ዓመት የጥበቃና የፅዳት የደንብ ልብስ እና የእጅ የስፌት ዋጋ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1 – የጥበቃና የፅዳት የደንብ ልብስ
- ሎት 2-የልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ
ኤጀንሲው ባወጣው ጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟለት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴትታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያቁጥር የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና፣በግዢ አቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅበቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለደንብ ልብስ ብር 10000/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ .
- ለስፌት የእጅ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000/ሶስት ሺህ ብር/በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ያስይዛል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት አገልግሎት መ/ቤቱ ባወጣውና ባዘጋጀው የፍላጎት መግለጫ መሠረት የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር /በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ። .
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡
- – ጨረታው በአየር ላይ በዋለ በ15ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው እለት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟለት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከኤጀንሲው ግዢ፣ ዳይሬክቶሬት ቢሮ 72 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል፣ ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በታሸገ ፖስታ ለየብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የኤጀንሲው አድራሻ፡- ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊትለፊት ::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-812-15-14 ይደውሉ፡፡
የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ