የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የመታወቂያ መሳሪያ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የመታወቂያ መሳሪያ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች የማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ የተዘጋጀውን የሥራ ዝርዝር (Specification) የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ዋናው /ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ቢሮ ቁጥር Go6 እየቀረቡ ሠነድ በመውሰድ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት በተደፈነ ኤንቨሎፕ ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሠነድ ለየብቻ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2012 . ከቀኑ 600 ሰዓት ድረስ ሠነዱን ከገዙበት ቢሮ ቁጥር Go6 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

ተጫራቾች በቅድሚያ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ስከበሪያ ብር 10,000.00 (አሥር ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከቴክኒካል ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው ኤንቨሎኘ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 1 ቀን 2012 . ከቀኑ 830 ሰዓት በድርጅቱ ማሠልጠኛ ክፍል Go6 ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ  መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-551-09-24

ወይም የበለጠ  መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011-51532-72 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት

ድርጅት