የመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ በ2012 በጀት አመት ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውል ቴትረን 6000 ጨርቅ፣ ቆዳ ጫማ፣ፕላስቲክ ቦት ጫማ፤ የተዘጋጁ ልብሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ 2012 በጀት አመት ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 • ሎት 1፡ ቴትረን 6000 ጨርቅ፤
 • ሎት2 ቆዳ ጫማ
 • ሎት 3 ፕላስቲክ ቦት ጫማ፤
 • ሎት 4 የተዘጋጁ ልብሶች

በመሆኑም በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልግ በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው ድርጅት ከዚህ በታች የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት እንድትወዳደሩ ኢንተርፕራይዙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
 2. የጨረታውን ፋይናንሽያል ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግ፤ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ እንዲሁም ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእያንዳንዱን ሎት ጠቅላላ ዋጋ 1% በኢንተርፕራይዙ የገቢ ደረሰኝ ወይም በመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ ስም ሲፒኦ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ ሰነዱን መንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ ሽያጭ ክፍል ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 50.00 (አምሳ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
 5. የጨረታ ጥሪው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ (ቅዳሜን ጨምሮ) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ ግዢ ክፍል ለዚህ ግዥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 6. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 1130 ላይ ታሽጎ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 300 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የማያግድ ከመሆኑም ባሻገር በጨረታ ሂደቱ ለተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
 7. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በበዓል ቀናት ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል፡፡
 8. አሸናፊው አካል ውጤቱ ከተገለፀለት ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (CPO) በማስያዝ በአምስት ቀናት ውስጥ በግንባር ቀርቦ የውል ስምምነት መውሰድ አለበት፡፡
 9. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0912165671 ወይም አካል መጥቶ ማናገር ይቻላል፡፡

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መንቆረር

አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ