የጨረታ ማስታወቂያ
የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የግዥ መለያ ቁጥር ግፋ/08/2012
የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በላይ በተገለፀው ዝርዝር መስፈርት መሠረት ቀርበው መውዳደር ይችላሉ።
በዚሁ መሠረት የሚፈለጉ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ቀርቧል።
ተ.ቁ |
መግለጫ |
መለኪያ |
ብዛት |
1 |
የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ዕቃዎች |
ቁጥር |
838 |
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የ2012 ዓ.ም የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የጨረታ ዋስትና መያዣ ብር 20000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ግዥውን በሚፈፅመው ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል ። ከተጠየቀው ሲፒኦ ማስያዣ ውጪ ያቀረበ ጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- የተዘጋጀውን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ፣ ንብ/አስ/ኬ/ቲ/አስተባባሪ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መምጣት አለበት ሠነድ ካልያዙ የጨረታ ዶክመንቱ አይሸጥም፤
- የዕቃዎች ብዛት ተዘጋጅቶ በሚሸጠው የጨረታ ዶክመንት ላይ በዝርዝር ተገልጿል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከ/መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የግዥ፤ንብ/አስ/ኬ/ቲ/አስተባባሪ በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥ ንብ/አስ/ኬ/ቲ/አስተባባሪ ይከፈታል። ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- በጨረታ መክፈቻ ዕለት ለሁሉም ሎት ሳምፕል ዕቃዎች ከአንድ በላይ አማራጭ ይዞ መቅረብ አለበት። በዕለቱ ሳንፕሉን ይዞ ያልተገኘ ተጫራች የጨረታ ዶክመንቱ ሳይከፈት ተመላሽ ይደረግለታል።
ስልክ ቁጥር 046-212-1580/ 046-221-28826
ፖ.ሣ.ቁ 108 አድራሻ ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ አስፋልት ፊት ለፊት
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት