የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ለቢሮና ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያና ኮምፒውተር ቀለም የቤተ መጽሐፍት ጠረጴዛ፣ የመማሪያ መጽሐፍቶች፣

የጨረታ ማስታወቂያ 

የግዥ መለያ ቁጥር HUCA/NCB 2nd/ 01,02,03/2012 BY 

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ለቢሮና ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ

 • ሎት 01፤ የጽህፈት መሳሪያና ኮምፒውተር ቀለም፣
 • ሎት 02 ፤ የቤተ መጽሐፍት ጠረጴዛ፣
 • ሎት 03፣ የመማሪያ መጽሐፍቶች፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 
 1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ግ/ን/አስ/የስ/ሂ/ቡድን መውሰድ ይችላሉ:: 
 2. ተጫራቾች የዘመኑን ዕድሳት የተከናወነበት በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌደራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለጽህፈት መሳሪያና ለኮምፒውተር ቀለም 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ለቤተ መጽሐፍት ጠረጴዛ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለመማሪያ መጽሐፍት ብር 30,000.00 / ሰላሳ ሺህ ብር / በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ስም ለእያንዳንዱ ሎት ከፍለው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ደረሰኙን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በኦርጂናልና ኮፒ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 05 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሀ/ዩ/ግ/ኮሌጅ ግ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ የተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ 
 5. ጨረታው ሚያዚያ 05 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ሚያዚያ 05 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ግቢ በሚገኘው ግ/ን/አስ/የስ/ሂ/ ቡድን ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 
 6. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የተጫረቱበትን ዕቃዎች ትክክለኛ ናሙና / GENUNE SAMPLE / ማቅረብ አለባቸው:: 
 7. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 046 220 47 40 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡ 
 8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ