የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በአዊ በደ/ጎንደር በደ/ወሎ እና በሰ/ሸዋ መስ/ዞኖች በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘውን በድምሩ 57,130.85 ሜ/ኩብ የባ/ዛፍና የፈ/ጽድ ቁም ደን ምርትን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

የቁም ደን ምርት የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በአዊ በደ/ጎንደር በደ/ወሎ እና በሰ/ሸዋ መስ/ዞኖች በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘውን በድምሩ 57,130.85 /ኩብ የባ/ዛፍና የፈ/ጽድ ቁም ደን ምርትን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ፡-

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የሽያጩ መጠን 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ለጨረታ የቀረበውን የቁም ደን ምርት ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
 3. ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫዎችን ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይቻላል፡፡
 4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ጨምሮ/ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመከፈል አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና /ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አረጋውያን ሕንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 እንዲሁም ምርቱ ካለባቸው //ቤቶች መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርት ለመግዛት የሞሉትን ጠቅላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) /ዳር ከተማ ቅርንጫፍ ባንክ ካላቸው ማናቸውም ባንኮች በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርት በኦርጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ተፈርሞ ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በማሸግ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና /ቤት /ዳር፣ በኮምቦልቻና /ብርሃን //ቤት የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀም በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት /ቅዳሜን ጨምሮ/ እስከ መጨረሻ ቀን 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 400 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የመጨረሻው ቀን የሕዝብ በዓላት ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
 7. ተጫራቾች የሚሞሉበት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
 8. ተጫራቾች ካቀረበ አንድ ክፍልፋይ በታች መጫረት አይችሉም፡፡
 9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0582263095 0582270635 0335510118 058441030 6 0116375030 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
 11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ

 ባሕር ዳር