በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሰቲ የመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ በ2011/2012 ምርት ዘመን በቡሬ እርሻ ልማት ፕሮጀክት ያመረተውን 970 ኩ/ል በቆሎ እና 13 ኩ/ል ሱፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሠብል ሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሰቲ የመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ በ2011/2012 ምርት ዘመን በቡሬ እርሻ ልማት ፕሮጀክት ያመረተውን 970 ኩ/ል በቆሎ እና 13 ኩ/ል ሱፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

በጨረታው ለመሳተፍ መሟላት ያባቸው፤ 

 

  1.  በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ስራ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ 
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ  ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር ብቻ) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ለሽያጭ የተዘጋጀውን ሠብል ቡሬ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ መጋዘን ድረስ በመቅረብ የምርት ናሙናውን መመልከት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚገዙትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% በኢንተርፕራይዙ የገቢ ደረሰኝ ወይም በመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ ስም ሲፒኦ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  6. የጨረታ ጥሪው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ (ቅዳሜን ጨምሮ) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ ግዢ ክፍል ለዚህ ግዥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ ታሽጎ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት የማያግድ ከመሆኑም ባሻገር በጨረታ ሂደቱ ለተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ 
  8. አሸናፊው አካል ውጤቱ ከተነገረው ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ የውል ስምምነት ይይዛል፤ በስምምነቱ መሰረትም ንብረቱን ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡ 
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

 መረጃ በስልክ ቁጥር 0912165671 ወይም በአካል መጥቶ ማናገር ይቻላል፡፡ 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመንቆረር አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ