የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል የጣሪያ ክዳን ቆርቆሮ (28ጌጅ) እና ጥራት ያላቸው የተለያዩ መጠን ያላቸው (የቆርቆሮ ባለቆብ ፤ባለ 8 ሴሜ፣ባለ 9 ሴሜ፣ባለ 10 ሴሜ፣ባለ 12 ሴ.ሜ) ሚስማር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

LGB/OEB/GOV/15/2012

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል የጣሪያ ክዳን ቆርቆሮ (28ጌጅ) እና ጥራት ያላቸው የተለያዩ መጠን ያላቸው (የቆርቆሮ ባለቆብ ፤ባለ 8 ሴሜ፣ባለ 9 ሴሜ፣ባለ 10 ሴሜ፣ባለ 12 .) ሚስማር ህጋዊ የሆኑ ከአምራች ድርጅት እና ብቃት ያላቸው ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልገና ዕቃውን ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ቦታ ማድረስ የምትችሉ ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ጋር፡-

  • በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ (clearance)፣የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPOብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማቅረብ አለባቸው ::
  • ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔስፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገፆች ላይ በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ  ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ በአንድ  ፓስታ ታሽጎ ከሳር ቤት ወረድ ብሎ በሚገኘው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 1 ፎቅ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን፣ስልክ ቁጥራቸውንና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስይህንን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ውስጥ ከተሸጠ በኋላ በ16ኛው ቀን እስከ 800 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት 8:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡
  • የጨረታው ዶክመንት በዚሁ እለት 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ይህ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ፤በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን 830 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • ቢሮው የተሻለ ዘዴ ወይንም አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::

 

ስልክ ቁጥር፡– 0113-69-01-89

ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ