በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል፡ የጽ/መሳሪያዎች ፡ የጽዳት እቃዎች ፡ የደንብ ልብስ ፡ ኤሌክትሮኒክስ እና ፡ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2012 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል፡፡

 • ሎት1 የጽ/መሳሪያዎች ፡
 • ሎት 2የጽዳት እቃዎች ፡
 • ሎት3የደንብ ልብስ ፡
 • ሎት 4ኤሌክትሮኒክስ እና ፡
 • ሎት 5የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 

ዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላ

 1.  የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን  ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)ያላቸው 
 3. የግዥው መጠን ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) እና በላይ ሲሆን ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ 
 4. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመኖራቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 
 5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
 6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ (ለሎት 1 ብር 1500)፤(ለሎት 2 ብር 500) (ለሎት 3 ብር 1000)፤ (ለሎት 4 ብር 5000) እና (ለሎት 5 ብር 4000) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ተዕዛዝ ሲ ፒ ኦ (CPO) ማቅረብ አለባቸው:: 
 7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (10) አስር ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል 
 8.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
 9. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ወቅት ሳምፕል ለመ/ቤታችን ማቅረብ አለባቸው:: 
 10. ከጥቃቅንና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ። 

አድራሻ፡ ቃሊቲ ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን ገባ ብሎ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 011471-79-31 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍስ ከተማ የወረዳ 7 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት