የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብርና ሌሎችንም የንግድ ታክሶች የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋዮች ከሆኑ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲያይዙ ይጠየቃሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘቡ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው እንደተገለፀላቸው 5 የሥራ ቀን በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በማስያዝ ከገዥ ጋር ውል ይፈራረማሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት በማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ::
  6. ተጫራቾች የመሸጫ ዋጋቸውን በሰም በታገዘ ኤንቨሎፕ በግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ድረስ ይዞ በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 230 እስከ 430 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 445 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት ከአዋሽ ባንክ ገባ ብሎ

በስልክ ቁጥር፡– 011-4-42-56-60, 011-4-40-04-60

የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ