በደቡብ ክልል እርሻና ተፈ/ህ/ል/ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ካተያዘው በጀት ለመማር ማስተማር ሥራ የሚውሉ የተለያዩ መሣሪያዎችን ማለትም ለደንብ ልብስ ተጠቃሚዎች የሚሆን ጫማ ኮንሱል ሸሚዝ ሱፍ ካፖርትና ፖሊስተር ጨርቅ፡ ቦብሊን ጨርቅ የፕሪንተር ቀለም፣ የተሽከርካሪ ጎማ፣ የተማሪዎች መመረቂያ መጽሔት፡ የተማሪዎች መመረቂያ ባይንደርን ጨምሮ በ3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

በደቡብ ክልል እርሻና ተፈ/ህ/ል/ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ካተያዘው በጀት

 • ለመማር ማስተማር ሥራ የሚውሉ የተለያዩ መሣሪያዎችን ማለትም
 • ለደንብ ልብስ ተጠቃሚዎች የሚሆን ጫማ ኮንሱል ሸሚዝ ሱፍ ካፖርትና ፖሊስተር ጨርቅ፡
 • ቦብሊን ጨርቅ የፕሪንተር ቀለም፣
 • የተሽከርካሪ ጎማ፣
 • የተማሪዎች መመረቂያ መጽሔት፡
 • የተማሪዎች መመረቂያ ባይንደርን ጨምሮ በ3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ : – 

 1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ 
 2. የዘመኑን የግብር ግምታጥወን የተወጡ፣ 
 3. የተ.እ.ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ 
 4. የቲን ሠርተፍኬት ያለው፣ 
 5. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው 
 6. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታወነ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ /ዶክመንት/ የማያምለስ ብር 100,00 /አንድ መቶ ብር/ በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ስም ተከፍቶ በሚገኘው አካውንት ቁጥር 1000018208443 በማስገባት የባንክ አድቫይስ በመያዝ ከወላይታ ሶዶ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦርጅናሉን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ ግብር ቴ/ሙ/ት/ሥኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 41 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥሪ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት 8፡30 ሰዓት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 ይከፈታል፡፡ 
 9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠለት ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝና የማይነበብ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ 
 11. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 12. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡ 
 13. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች እስከ ኮሌጃችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 551 3984 ደወለው ማነጋገር ይቻላል፡፡ 

በደቡብ ክልል እርሻና ተፈ/ሀ/ል/ቢሮ 

የወላይታ ሶዶ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ