በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ/ሀዲያ ዞን የሆሣዕና ከተማ አስ/ጤና ጥ/ጽ/ቤት ሥር የሚገኝ ሆ/ጤ/አ/ጣቢያ የህንፃ ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ 

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ/ሀዲያ ዞን የሆሣዕና ከተማ አስ/ጤና ጥ/ጽ/ቤት ሥር የሚገኝ ሆ/ጤ/አጣቢያ የህንፃ ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሰረት ፡

  1. ደረጃቸው BC-7 GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፡- የንግድ ምዝገባ ፈቃድ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከሆሣዕና ከተማ ጤና ጣቢያ ግዥ ፋይናንስ/ን/ አስተዳር ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስክ 30ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል 
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሆሣዕና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ስም 15,000/አሥራ አምስት ሺህ ብር/በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በፖስታ በሰም አሽጎና ማህተም በማድረግ ፈርሞ ማቅረብ አለባቸው:
  3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሰሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ሦሥቱንም ሰነዶች በሌላ እንድ ማጠቃለያ ፖስታ አሽጎና የፕሮጀከቱን ስም ጠቅሶ እና የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል ሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒ ሰነዶች እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጅናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder certification of Compliance) ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ ሰሰም አሽጎና ሁለቱንም አቃፊ ማለትም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል አቃፊ ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል።የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ(Bidder Certification of compliance) በየመጠየቁ (ባዶ ቦታዎች ተሞልቶ፣ ተፈርሞና ታሽጎ መመለስ አለበት።የቴክኒካል ሃሳብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ያለመመለስ ከወድድር ውጭ ያደርጋል።
  4. ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤ/አጣቢያ የመሰባሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።ጤና ጣቢያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

ማሳሰቢያ፡-ከዚህ በፊት በዞኑ ውስጥም ሆነ በከተማ ውል ገብተው የግንባታ ሥራ እየሠሩ በውል ጊዜ ያለበቂ ምክንያት ያላጠናቀቁ የሥራ ተቋራጮች ጨረታው ላይ መሳተፍ አይችልም:: ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ከገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ ጤ/ ጣቢያው ለሥራው ውል ለመግባት አይገደድም 

ጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 555 2554 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። 

 

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ሀዲያ ዞን የሆሣዕና ከተማ አስ/ጤና/ጥ/ጽ/ቤት