የጨረታ ማስታወቂያ
ግ.ጨ.ቁ ESLSE/PAGS/
NCB/35/2012
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎችን ማቅረብ ከሚችሉ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች በማሟላት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- በዘርፉ የተሠማሩ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ የተእታ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጊዜው ያላለፈበት የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያሳይ በመረጃ (tax_clearance) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እንዲህ በአቅራቢዎች ዝርዘር የተመዘገበ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲሁም ከአምራች የሚሰጥ ፍቃድ (authorization letter) ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ፖስታው ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታ በመለየት በተናጠል መቅረብ አለበት ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከ2% ያላነሰ ወይም ከ500,000 ብር ያልበለጠ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ “የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ለጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት” በሚል ስም በማሰራት መቅረብ አለበት::
- የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ለገሐር በሚገኘው የቀድሞ የማሪታይም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ቢቁ/o6 በሚገኘው የፋይናንስ ክፍል ቢሮ መውሰደ ይቻላል፡፡
- ጨረታው “በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት” አዲሱ ህንፃ 10ኛ ፎቅ ሚያዝያ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ሚያዝያ 8 ቀን 2012 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ፖስታው ይከፈታል::
- ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር፡ 011554 97 81/86
Website: www.ethiopeanshippinglines.com.et
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና
ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት