የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በጨፋሮቢት ከተማ በ2012 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት ለሚያሠራው የ G+3 ቢሮ ግንባታ ህጋዊ የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ፈቃድ ካላቸው ላይ በሙሉ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በጨፋሮቢት ከተማ በ2012 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት ለሚያሠራው የ G+3 ቢሮ ግንባታ ህጋዊ የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ፈቃድ ካላቸው ላይ በሙሉ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2012 .

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ////ቤት በጨፋሮቢት ከተማ 2012 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት ለሚያሠራው G+3 ቢሮ ግንባታ ህጋዊ የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ፈቃድ ካላቸው ላይ በሙሉ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡

 1. ተጫራቾች ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም  ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ምስክር  ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ሊያቀርቡ ይገባል፡፡
 4. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈለና ይህንኑ የሚያመላክት ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
 5. የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
 6. TIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
 7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሃሳብ መስጫ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን እና መሀተም ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
 8. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ  ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
 9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ሆኖ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
 10. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500 ብር በመክፈል የካፊያና ሂሳብ ደጋፊ የሥራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ፡፡
 11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 30/8/2012 . ለተከታታይ 21 ቀናት አየር ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
 12.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን 30/8/2012 . ከጠዋቱ 430 ///////ቤት ቢሮ ቁጥር  01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 23ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግሥት የሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ የሞሉትን ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንት (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 13. የቴከኒክ መወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጂናሉን ገላጭ በሆነ መንገድ በአንድ ፖስታ ኮፒውን ገላጭ በሆነ መንገድ በሌላ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም በሌላትልቅ  ፖስታ በማሸግ የፋይናንሽያል የመወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጂናሉን ገላጭ በሆነ  መንገድ በአንድ ፖስታ ኮፒውን ገላጭ በሆነ መንገድ በሌላ ፖስታ በማድረግ  ሁለቱንም በሌላ ትልቅ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን በአንድ  ፖስታ በማድረግ ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች በሌላ ትልቅ ፖስታ አንድ ላይ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 14. የጨረታ ማስገቢያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሠነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል፡፡
 15. /ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡

 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0334490340/ 0334490061/ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • አድራሻችን ጨፋሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 300 / ላይ እንገኛለን፡፡
 • ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የሰነዱን ዓይነት፤ የግንባታውን ቦታ፤ የአሠሪውን ባለቤት ስም መግለጽ፤ የግንባታውን ስም፤ ኮፒ ወይም ኦሪጂናል፤ የቴክኒክ ወይም የፋይናንስ ዶኩመንት መሆኑን በግልጽ ማሳየት መቻል አለባቸው።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን

የአርጡማ ፋርሲ ወረዳ ////ቤት