በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 006/2012 

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 

NO.

Items

Quantity

1

Basic life support ambulance

3

2

Mobile workshop

2

3

Firefighting truck

2

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

 1. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት። 
 2. ተጨማሪ እሴት ታክስ /ባት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ። 
 3. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ። 
 4. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (Tin number) ያላቸው። 
 5. የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ። 
 6. ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ሀዋሳ ደ/ብ/ብ/ህ/ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 304 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል። 
 7. ጨረታው በጋዜጣታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይውላል። 
 8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው አየር ላይ መዋያው ጊዜ ባበቃበት ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል: 
 9. ተጫራቾች ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው: 
 10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያሰፈልጋቸው ስልክ ቁጥር 0462207835/ በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0462204499 ማግኘት ይችላሉ። 
 11. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡ 

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ 

ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት 

ማስወገድ አገልግሎት 

ሀዋሳ