የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የተለያዩ ዕቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Tender
< Back

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የተለያዩ ዕቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የማስታወቂያ ቁጥር ብግጫ/02/2012 

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከዚህ በታች በሎት  የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

ምድብ

የዕቃው ዓይነት 

ሎት 1

የቢሮ የፅህፈትና የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎች(Common Items) 

ሎት 2

የቢሮ የፅዳት መጠበቂያና መገልገያዎች 

ሎት 3

የተሽከርካሪ መኪናዎች የፅዳት መጠበቂያና እና አልባሳት ዕቃዎች 

ሎት 4

ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች 

 በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች  የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው። 

  1.  በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ 
  2. የታክስ እና የግብር ግዴታቸውን የተወጡና የቲኢቲ ከፋይ 
  3. የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፍኬት 
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ 3000 (ሶስት ሺህ ብር) .
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከባለስልጣን መ/ቤቱ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 903 መግዛት ይችላሉ። 
  6. ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜ እና ዕሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ የጨረታ መክፈቻው ቀን በሚቀጥለው ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  7. ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

 መረጃ፡- የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባስስልጣን ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ህንፃ 9ኛ ፎቅ ቢሮ 

ቁጥር 903 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 

ቁጥር 0115314016/0115314113 መጠየቅ ይቻላል። 

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባስስልጣን