የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ በህንፃ እድሳት ወቅት የወላለቁ ብረቶች፣ የእንጨት በሮችና ፓርቲሽኖች እንዲሁም ንቃይ ቆርቆሮዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ በህንፃ እድሳት ወቅት የወላለቁ ብረቶች፣ የእንጨት በሮችና ፓርቲሽኖች እንዲሁም ንቃይ ቆርቆሮዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ 

ቁርጥራጮች ብረቶች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ በህንፃ አድሳት ወቅት የወላለቁ ብረቶች ፣የእንጨት በሮችና ፓርቲሽኖች እና ንቃይ ቆርቆሮዎች ሽያጭ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ በህንፃ እድሳት ወቅት የወላለቁ ብረቶች፣ የእንጨት በሮችና ፓርቲሽኖች እንዲሁም ንቃይ ቆርቆሮዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ። 

  1.  በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንን የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። 
  2. ተጫራቾች የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊትለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር 2 ውስጥ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኮርፖሬት አገልግሎቶች ቢሮ በመምጣት የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውስድ ይችላሉ። 
  3.  ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት(ቅዳሜን ሳይጨምር) ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ኮተቤ መንገድ ከአራራት ሆቴል አለፍ ብሎ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ። 
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ንብረቶች ለእያንዳንዱ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በተመከተው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። 

/

የእቃው ዓይነት 

መለኪያ

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር 

1

ቁርጥራጭ ብረቶች 

በኪሎ 

30,000.00/ሠላሳ

2

ጎማ 

በቁጥር 

10,000.00/አስር ሺህ 

3

ባትሪ 

በቁጥር 

3,000.00/ሶስት

4

የህንፃ ፍርስራሽ ብረቶች

በኪሎ 

30,000.00/ሠላሳ

5

የእንጨት በሮችና ፓርቲሽኖች

በጥቅል

3,000.00/ሶስት

6

ንቃይ ቆርቆሮዎች 

በቁጥር 

3,000.00/ሶስት

5. ተጫራቾች የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርትና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል። ይህን እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል። 

6.የጨረታ ሣጥኑ ሚያዚያ 20 ቀን 2012 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም። 

7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸውን በተገለፀላቸው ከ 7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ያደርጋል። 

8. ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል። 

9. አሸናፊ ተጫቾች ያሸነፉባቸውን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። 

10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0118965521 ወይም 0118965522 ደውሎ መጠየቅ ይችላል። 

11. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ 

አድራሻ፡- የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊትለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 08/09 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ