የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን የዳታ ሴንተር ጥገና እና ተዛማች ዕቃዎች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን እና አቅምና ብቃት ያላቸው አቅራቢዎች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Tender
< Back

የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን የዳታ ሴንተር ጥገና እና ተዛማች ዕቃዎች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን እና አቅምና ብቃት ያላቸው አቅራቢዎች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 02/2012

ባለስልጣን መ/ቤታችን የዳታ ሴንተር ጥገና እና ተዛማች ዕቃዎች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን እና አቅምና ብቃት ያላቸው አቅራቢዎች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩ እና የ2012 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣ የመንግስት ዕቃ አቅራቢ ስለመሆናቸው የገንዘብ ሚኒስቴር (PPA) ዌብሳይት ምዝገባ ያከናወኑ ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ግብር ከፋይ መለያ ምዝገባ ሰርተፍኬት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢ ድርጅቶች:

  • የጨረታ ሰነዱን በግ/ፋ/ን/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ቀርበው የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፤ በእስፔስፊኬሽኑ (በናሙናው መሰረት) በተገለፀው የዕቃ ዓይነት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሀሳባችሁን በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በመለየት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ 3000.00 (ሦስት ሺ) ብር በባንክ በተመሰከረት ቼክ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፤
  • ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ 07 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ይዘጋና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • 15ኛውና 16ኛው ቀናት ከእረፍት በበዓላት ቀን ከዋለ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ከላይ በተገለፀው ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፤
  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዝቅተኛ ዋጋ እና ቴክኒካል ብቃት ይወዳደራሉ::
  • ባለስልጣኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

አድራሻ ፌ.አ.መ.ማ.ኢ.ማ.ባ ሜክሲኮ አደባባይ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት/ አዲስ አበባ

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ለባለስልጣኑ መረጃና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት

በስልክቁጥር ፡- 011-551 11 22/011-51551 86 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን