የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ፡ የቫት ደረሰኝ እና የቫውቸር ደብተር ህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

Tender
< Back

የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ፡ የቫት ደረሰኝ እና የቫውቸር ደብተር ህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

የህትመት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ 

የግዢ መያ ቁጥር CC/NCB/ P/S/20/2012 

የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች:-ሞዴል-265፡ሞዴል 266 ፡ ሞዴል-270 ፡ የቫት ደረሰኝ እና የቫውቸር ደብተር ህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሰረት ዝርዝር ሁኔታውን በፍላጎት መግለጫ ዝርዝሮችና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጾች ላይ በቀረቡት ዝርዝር የአፈጻጸም ሰነዶች መሰረት ይሆናል ። 

 1.  በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ 
 2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርብ 
 3. ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
 4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ 
 5. እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ቀርበው የማይመለስ 100 /አንድ መቶ/ ብር በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ከዴሉክስ ፈርኒቸር አጠገብ በሚገኘው የኮሚሽኑ ግዢ ክፍል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 7. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በሚያበቃበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስአት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ 
 8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 5 ሺህ ብር ሲፒኦ ወይንም በሁኔታላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ስም በማሰራት ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 9. ተጫራቾች ኣሸናፊ ሆነው ውለታ ሲፈጽሙ የውለታ ማስከበሪያ ባሸነፉበት ዋጋ ልክ 10 ፐርሰንት ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል 
 10. ተጫራቾች እስከተቻለ ድረስ ዋጋ ማቅረብ ያለባቸው መ/ቤቱ በሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚለው ቦታ ላይ ቫትን ተ.እታ/ ያካተተ ዋጋ በመሙላት መሆን . ይኖርበታል፡፡ 
 11. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካል 1 ኦሪጅናል ፣ ኮፒ፣ ፋይናሺያል አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በድምሩ 4 የመወዳደሪያ ፖስታዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ። 
 12. ኮሚሽኑ በሚያከናውናቸውግዢዎች ላይ 20 ፐርሰንት የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው 
 13. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

ኣድራሻ፡- ሲኤምሲ ሚካኤል ፊትለፊት ከዴሉክስ ፈርኒቸር አጠገብ ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 ግዢና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-878-79-91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ