የወሊሶ ከተማ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለከተማው የመንገድ ላይ ማብራት አገልግሎት የሚውል የማብራት ሥራ (LED Street Light Work) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Tender
< Back

የወሊሶ ከተማ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለከተማው የመንገድ ላይ ማብራት አገልግሎት የሚውል የማብራት ሥራ (LED Street Light work) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Waliso-IR-CW-001-2012

የወሊሶ ከተማ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለከተማው የመንገድ ላይ ማብራት አገልግሎት የሚውል የማብራት ሥራ (LED Street Light work) Package- Number- Waliso –IR-CW-001-2012 የሆነውን ከነ ሙሉ አክሰሰሪ እና ፖል ተከላ እንዲሁም ኢንስታሌሽን ጭምር በዘርፉ የተሰማሩትን ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው፣ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ (For EM/GC 5 and above) ያላቸው፣ ተመሳሳይ የስራ ልምድ ያላቸውና ለሽያጭ በተዘጋጀው ዶክመንት ውስጥ የተገለጸውን መስፈርት (must meet requirement) የሚያሟሉትን ድርጅቶችን በመንግስት የግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ በተገለጸው መመሪያ መሰረት  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች

ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ስለ ስራው የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወሊሶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሒሳብ ቁጥር 1000207507559 በመክፈል በወሊሶ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ደረሰኝ በመቁረጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የተጫራቾች መመሪያ

 1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ሙሉ የግንባታ ስራ ፈቀድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት (VAT) ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ :: በአንድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አንድ ሰነድ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ቋሚ  አድራሻ ያላቸው፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ የግንባታ ግዥ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ 2% CPO በወሊሶ ከተማ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ማቅረብ የሚችሉ (ቢቻል በወሊሶ ከተማ ውስጥ ባሉት ባንኮች ቢሆን ይመረጣል) ፡፡
 5. ተጫራቹ ማጭበርበር ፣ ሙስና፣ማታለልና የማስገደድ ድርጊት የማይፈጽም መሆኑን ለማረጋገጥ ግዴታ ለመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ቅጽ ሞልተው በመፈረም ማስገባት አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትንዋጋያለስርዝ ድልዝ በጨረታው ሰነድላይ በዶክመንቱ ውስጥ በተገለጸው መሰረት እያንዳንዱን በጥንቃቄ በመሙላት የቴክኒክ ሰነድ አንድ ኦርጅናል ከሁለት ከፒ እና የፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል ከሁለት ከፒ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማስገባት በማሸግ ሙሉ መረጃን በፖስታ ላይ በመፃፍ በመፈረም፣ስም በመፃፍ፣የፈራሚውን ስልጣን በመፃፍና በማህተም በማረጋገጥ በተጨማሪ የታሸገውን የቴክኒክና የፋይናንሽያል ሰነዱን በትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማስገባት በማሸግ ሙሉ መረጃን በእያንዳንዱ አንድ አንድ በታሸጉት ፖስታ ላይ በመሙላት በመፈረም፣ስም በመፃፍ፣የፈራሚውን ስልጣን በመፃፍና በማህተም በማረጋገጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በወሊሶ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ሰነዱን ገዝተው ከላይ በተገለጸው ቀን መሰረት ያላስገባ ተጫራች ከውድድሩ የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
 7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የሚያስገቡት መረጃ ደምቆ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፡፡ ደምቆ የማይታይና ስርዝ ድልዝ ያለበትን መረጃ ያስገባ ተጫራች ኃላፊነቱ የራሱ ይሆናል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቶች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 21ኛ ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰውን የመመዘኛ መስፈርትን በማሟላት በመጀመሪያ ግምገማ የቴክኒክ ግምገማን አልፈው የፋይናንሽያል ግምገማን ያለፉ ከሆነ አሸናፊ ይሆናሉ፡፡ የቴክኒክ ግምገማን ያላለፉ ተጫራቶች ያስያዙት CPO ና የፋይናንሽያል ሰነዳቸው ሳይከፈት ይመለስላቸዋል፡፡
 11.  ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- (011-341-3012/011-341-1914) በመደወል  መረዳት ይችላሉ፡፡

የወሊሶ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት