የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎቶች ላይ መሰማራት የሚፈልጉ አመልካቶችን አወዳድሮ የሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል፡፡

Tender
< Back

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎቶች ላይ መሰማራት የሚፈልጉ አመልካቶችን አወዳድሮ የሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል፡፡

የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት 

አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት የወጣ ድጋሚ 

የጨረታ ማስታወቂያ 

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 533/99 አንቀጽ 7(2) በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በአማርኛና በተለያዩ ቋንቋዎች በሚሰራጩ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎቶች ላይ መሰማራት የሚፈልጉ አመልካቶችን አወዳድሮ የሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል፡፡ 

በዚህ መሰረት፡-

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚሰራጭ የንግድ ኤፍኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 97.5፣104.1፣ እና 98.7 ሜጋ ኸርዝ (MHz) ሬዲዮ ሞገዶችን ዝግጁ አድርጓል፡፡ 

በመሆኑም የንግድ ኤፍ ኤም ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለማግኘት መወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 45 (አርባ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዮዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 601 ቀርቦ የፈቃድ ማመልከቻ ቅጽ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመከፈልና በባለሥልጣኑ የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ ወስዶ በመሙላት፣ የመወዳደሪያ ፕሮጀክት ሰነድ እንዲሁም ለውድድሩ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ከማመልከቻ ቅጹ ጋር በማያያዝ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የአመልካቾች የመወዳደሪያ ፕሮጀክት እና የአመልካቾቹን 

  1. የፋይናንስ አቅምና ተአማኒነት፣ 
  2. የመሳሪያዎች የቴክኒክ ጥራት፣ 
  3. ድርጅታዊ ብቃት፣ 
  4. የሰው ሀብትና የስራ ልምድ፣ 
  5. የፕሮግራም ይዘትና መርሃግብር፣ 
  6. በፕሮግራሙ የተካተቱ ማህበራዊ ፍላጎቶች እና 
  7. ለአገልግሎቱ የተመደበውን የስርጭት ጊዜ ማካተት ይኖርበታል፡፡ 

ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በታተመ በ46ኛው ቀን በባለሥልጣኑ የመሠብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0115-53-87-55-56/0115-53-87 65/66/60 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

የኢትዮጵያ ብሮድካስት 

ባለሥልጣን